የእምነት ባህርይ

በየዕለቱ እምነትን እንለማመዳለን፡፡ ከምናምንበት ነገር ወይም ዋጋ ከምንሰጣቸው ነገሮች ዘጠኛ ዘጠኝ በመቶ ያህሉ ከእምነት የሚመነጩ ናቸው፡፡ እምነት የሕይወት ሁሉ ማዕከል ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ታመማችሁ እንበል፡፡ ስሙን በትክክል ወደማታውቁትና የተቀበለውን ዲግሪ ትክክለኛነት ወዳላረጋገጣችሁት ሐኪም ትሄዳላችሁ፡፡ ምናልባትም እናንተ በቀላሉ የማታነቡን መድኃኒት ማዘዣ ይሰጣችኋል፡፡ በግል ወደማታውቁት የፋርማሲ ባለሙያ ትወስዱና እርሱም በቀላሉ የማትረዱትን ኬሚካል የተሸከመ እንክብል ወይም ሌላ አይነት መድኃኒት ይሰጣችኋል፡፡ እናንተም ወደ ቤታችሁ ትወስዱና በማዘዣው መሠረት ትወስዱታላችሁ፡፡ ይህንን ሁሉ ስታደርጉ ሁሉን ነገር ከልባችሁ አምናችሁ ነው፡፡ እምነት ለክርስትና ሕይወትም ማዕከላዊ ነው፡፡ እምነት የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 232 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

እምነት ምንድን ነው?

በመጀመሪያ፣ እምነት ያልሆነውን ነገር ብነግራችሁ ጠጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

  • እምነት ስሜት አየይደለም፣ ማለትም፣ ስለ እግዚአብሔር ጥሩ የሚሰማው መሆን አይደለም፡፡
  • እምነት እውነታን ደፍጥቶ በእውር ድንብር በጨለማ ውስጥ መዘፈቅ አይደለም፡፡
  • እምነት በሕይወትህ እንዲሆንልህ የምትፈልገውን ነገር እንድታገኝ የሚያስችልህ ዓለም አቀፋዊ የማስገደድ ኃይል አይደለም፡፡ (ማለትም፣ በከዋክብት ጦርነት ወቅት የሚገለጥ ኃይል -- ሉቃስ ኃይልን ተጠቅሟል! )

የሚያሳዝነው ግን፣ በዚህ ዘመን አንዳንድ ክርስቲያኖች እነዚህን ሃሳቦች ያስተምራሉ፡፡

ሃንክ ሃኔግራፍ (Hank Haanegraff Christianity in Crisis) በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ የስኳር ህመምተኛ የሆነውን ልጃቸውን ኢንሱሊን እንዳይወስድ ያቋረጡትን የ ላሪ እና ላኪ ፓርከር የተባሉ ቤተሰቦች ታሪክን አስፍሯል፡፡ ያቋረጡትም፣ እምነት ብቻ ቢኖራችሁ (ግግም ብትሉ እንደማለት አይነት የሆነ እምነት ቢኖራችሁ) ይፈወሳል ተብሎ ስለተነገራቸው ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን፣ ልጃቸው በስኳር ህመሙ ምክንያት ኮማ ውስጥ ገብቶ ሞተ፡፡ ከዚያም በኋላ የቀብር ሥነ-ስርዓት ከማዘጋጀት ይልቅ፣ የትንሣኤ ፕሮግራም አዘጋጁ፡፡ ያም ማለት ምንም ሳይራጠሩ፣ በቂ እምነት አንግበው፣ በጎ በጎ ነገር እየተናገሩ ይሆናል ብለው ቢያምኑ፣ የእምነት ኃይል ልጃቸውን ከሞት ያስነሣዋል ብለው ማመን ነበር፡፡ የኃላ ኋላ ግን ላሪና ላኪ ፓርከር የሰው ነፍስ በማጥፋትና ልጅን በማሰቃየት ተጠያቂ ሆኑ፡፡ ለምን? ምክንያቱም ስለ እምነት የተሳሳተ ሃሳብ ነበራቸውና ነው፡፡

በአዲስ ኪዳን የሚገኙ ወንጌላት (ማቴዎስ፣ማርቆስ፣ ሉቃስ እና ዮሐንስ) ደቀመዛሙርቱም ስለ እምነት ነገር ግራ ይጋቡ እንደነበር ያሳዩናል፡፡ ሆኖም፣ ስለ ጉዳዩ ኢየሱስን በጥበብ ይጠይቁት ነበር፡፡ በሉቃስ፣ ምዕራፍ 17 ውስጥ፣ እምነትን እንዲጨምርላቸው ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ይጠይቁታል፡፡ ኢየሱስ የመለሰላቸው ምላሽ ይኸውልህ፡

“የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፣ ይህን ሾላ ተነቅለህ ወደ ባህር ተተከል ብትሉት ይታዘዝላችሁ ነበር፡፡” የኢየሱስ ምላሽ አስገራሚ ነው፡፡ እኛ አሁን አሁን በቤተክርስቲያን እንደምናዘወትራቸው ዓይነት ነገሮችን አልተናገረም፡፡ ኢየሱስ “ጠንክራችሁ ሞክሩ” አላለም፡፡ ወይም ኢየሱስ፣ “በቃ እመኑ” አላለም፡፡ የኢየሱስ ምላሽ ስለ እምነት ምንነት እጅግ ወሳኝ እውነታን ገልጧል፡፡ የሰናፍጭ ፍሬ ከፍሬዎች ሁሉ አነስተኛ ናት፡፡ ኢየሱስ በዚህ ስፍራ እጅግ ወሳኝ የሆነ እውነታን አጉልቶ አውጥቷል ያም ወሳኙ ነገር የእኛ እምነት የግዝፈቱ መጠን አይደለም ነው፡፡ ይልቁኑ.. የእምነት ኃይል የሚያርፈው በታመነበት ነገር አስተማማኝነት ላይ ነው እንጂ እናንተ ምን ያህል ታመናችሁ በሚለው ላይ አይደለም፡፡

ምን ማለቴ እንደሆነ ላብራራ፡፡ በሰሜን ምሥራቃዊው የአሜሪካ ክፍል በቀዝቃዛው ክረምት የመጀመሪያ ሳምንት በአንድ ሐይቅ ዳር ቆሜ ነበር፡፡ በጣም ቀጭን በሆነች የበረዶ ግግር ሐይቁ ቅዝቅዝ ብሎ ነበር፡፡ አዲስ በተዘረጋው የበረዶ ግግር ላይ ለመራመድ የእምት እርምጃ ወሰድሁ፡፡ ምንም እንኳን በልበ ሙሉነትና “በሙሉ እምነት” ውጤቱ ግን እጅግ ሰቅጣጭ የሆነ ቅዝቃዜ ውስጠጥ መዘፈቅ ነበር፡፡ የበረዶው ግግር ቀጭን እስከሆነ ድረስ፣ የቱንም ያህል መጠን ያለው እምነት ቢኖረኝም ውጤቱን አየይለውጠውም፡፡ በረዶው ሊታመኑበት የሚችል አይደለም፡፡

ቀዝቃዛው ክርምት በደንብ ጫን ካለ በኋላ፣ ምን ሊሆን እንደሚችል እስኪ ገምቱ፡፡ በባህሩ ዳር ስቆም አሁን በረዶው በርካታ ኢንቾችን ወፍሮ ነበር፡፡ ቀደም ብሎ በገጠመኝ ችግር ምክንያት፣ በበረዶው ላይ ለመራመድ ሳስብ በጣም በጥንቃቄ ነበር፡፡ በረዶው ይሸከመኝ አይሸከመኝ እርግጠኛ አልነበርኩም፡፡ ቀድሞ ጉድ አድርጎኛል፡፡ ቀድሞ ካደረግሁት ይልቅ አሁን በጣም ብፈራም “እምነቴም አነስተኛ” ቢሆንም፣ በትልቅ ጥርጣሬ የምሰነዝራት አንድ እርምጃ አስተማማኝ መቆሚያ እንዳለኝ ታረጋግጥልኘኝ ነበር፡፡ ልዩነቱ ምንድን ነው? አሁን የምረግጠው ነገር ይበልጥ አስተማማኝ ነበር፡፡

የእምነት ኃይል የሚርፈው በሚታመኑት ነገር አስተማማኝነት ላይ የመሆኑ ነገር እውነት ነው፡፡ ሆኖም …

አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ የሚኖረው እምነት መጠን ያመነውን በማወቁ መጠን ልክ ነው፡፡

ለምሳሌ፣ አንድ መብረር የሚስጨንቀውን ሰው አስቡ፡፡ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአካባቢው ከሚያገኘው ወቅታዊ የኢንሹራነስ ካሳ መክፈያ ሳጥን ይሄድና የሚፈለገውን መጠን በማሽኑ ጨምሮ ኢንሹራንስ ይገዛል፡፡ አውሮፕላኑ ከመነሳቱ ሃያ ደቂቃዎች አስቀድሞ የመታጠቂያ ቀበቶውን ያስራል ከዚያም የተለመዱትን “የድንገተኛ አደጋ ጊዜ መውጫዎችን መመሪያዎች” በጥንቃቄ ያዳምጣል፡፡ አውሮፕላኑ ወደሚፈልገው መድረሻ ሊደርሰው ይቻል አይቻል እምነት የለውም፡፡ ሆኖም፣ በረራው ወደፊት ሲገፋ፣ መንገደኛው መለወጥ ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ የመታጠቂያ ቀበቶውን ይፈታል፣ ከዚያም ምሳ በጥቂቱ ይበላል፣ ብዙም ሳይቆይ አጠገቡ ከተቀመጠው ሰው ጋር መጨዋወትና መቀለድም ይጀምራል፡፡ ለውጡን ምን አመጣው? ምን ተከሰተ? 36000 ጫማ ላይ ሲደርስ ብዙ እምነት አገኘ? ፍፁም አይደለም፡፡ እምነቱ ያረፈበትን ነገር፣ የአውሮፕላኑን ምንነት ይበልጥ ሲያውቅ፣ በእርሱ ላይ እምነቱ እየጨመረ ሄደ፡፡

በክርስትናም ሕይወት ነገሩ ያው ነው፡፡ ስለ ጌታ ይበልጥ ስናውቅ፣ በእርሱ ላይ ብዙ እምነት እንጥላለን፡፡ ከስሜቶችህ ይልቅ በእግዚአብሔር ቃል እውነታዎች ላይ ተደግፎ መኖርን ተለማመድ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉትን እውነቶች በመመልከት፣ ይበልጥ ማንነቱን እንዲገልጥልህ በመለመን ጥሩ ጊዜ አሳልፍ፡፡ ለመነሻ ሊሆኑህ የሚቸሉ በርካታ ስፍራዎች አሉ፡፡ መዝሙር 145፣ 146 እና 147 የእግዚአብሔርን ማንነት የሚገልጡ አስደናቂ ምዕራፎች ናቸው፡፡ ከጠቅላላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ስለ ራሱ እንዲያስተምርህና በተለይም በእርሱ እንዴት ልትታመንበት እንደትቸል እንዲያሳይህ ለምነው፡፡ “በዚህ ሁኔታ ውስጥ አንተን ስታመን ስለ አንተ የትኛው ነገር ባውቀው ይጠቕመኛል ትላለህ?” ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቀው፡፡ ወደ መጽሐፍ ቅዱስህ ሂድና የእግዚአብሔርና ከእርሱ ጋር ያለህ ግንኙነት ተማሪ ሁን፡፡

በአንድ ወቅት ዲ.ኤል.ሙዲ እንዲህ አሉ፣ “እግዚአብሔር እምነት እንዲሰጠኝ በየቀኑ እጸልይ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ‘እምነት ከመስማት ነው፣ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡’ የሚለውን ሮሜ 10፡17 አነበብሁ፡፡ ስለዚህም፣ መጽሐፍ ቅዱሴን ማንበብ ጀመርሁ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በልዩ መንገድ የዲ.ኤል.ሙዲ እመነት ያድግ ጀመር፡፡”