ይህኛውስ ይዘልቅ ይሆን?

ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ዝምድና አስተማማኝ እንደሆነ እንዴት እናውቃለን?

በሕይወታችን ብዙም ሳይርቁ የተቋረጡ ብዙ ዝምድናዎች ነበሩን፡፡ ፍቺ፣ መስመር የለቀቁ ጓደኛማማችነቶች፣ ምናልባትም አንድ የምንወድደው ሰው በሞት መለየትም ሊሆን ይችላል፡፡ እናም፣ ከእግዚአብሔር ስለ ጀመርከው ስለዚህኛው ግንኙነትም ግር ሊልህና… ይህኛውስ ይዘልቅ ይሆን ብለህ ታስብ ይሆናል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ብሎናል፣ “… አልለቅህም ከቶም አልተውህም” (ዕብራውያን 13፡5) ይህም እውን የሚሆነው፣ እምነታችንን በኢየሱስ ላይ ስናደርግ፣ በሕይወታችን ታስፈልገናለህ ስንለው፣ እና ልጆቹ ሆነን በእርሱ ፍቅር ውስጥ እርፍ ብለን ለዘላለም በዋስትና ስንኖር ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ልንገዛው አንችልም፣ ወይም የራሳችን ለማድረግ መፍጨርጨር አይገባንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ግልፅ ነው፡፡ አንድ ጊዜ እምነታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ካደረግን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን እናገኛለን፡፡

“እርሱም፣ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ፡፡” (ሮሜ 3፤22-24)

የሚቀጥለው የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል ከእርሱ ጋር ካለህ ግንኙነት አንፃር አሁን እውነት የሆነውን እንድታይ ያግዝሃል፡

ክርስቲያን ከመሆናችን አስቀደሞ

ምናልባት ለሚከተሉት እንግዳ አታውቁ ይሆናል፡፡ ሆኖም፣ ክርስቲያን ከመሆናችን አስቀድሞ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እኛን እንዲህ ይገልፀናል፡

  • የእግዚአብሔር ጠላቶች (ሮሜ 5፡10)
  • ተስፋ ቢሶች (ሮሜ 5፡6)
  • ያለ እግዚአብሔር (ሮሜ 5፡6)
  • ኃጢአተኞች (ሮሜ 5፡8)
  • የጠፉ (ማቴዎስ 18፡11)
  • ድሆች (ራእይ 3፡17)
  • እውራን (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4)
  • ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች (ዮሐንስ 3፡36)
  • በኃጢአታችን ሙታን (ኤፌሶን 2፡1)
  • ሞኞች፣ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ ባሪያዎች (ቲቶ 3፡3)
  • ክፉውን የምናደርግ (ቆላስይስ 1፡21)
  • ከእግዚአብሔር የራቅን (ኤፌሶን 2፡13)
  • ተስፋ ቢሶች (ኤፌሶን 2፡12)
  • በጨለማ የምንመላለስ (ዮሐንስ 8፡12)

አሁን ደግሞ ክርስቲያን ነን

ክርስቶስን ወደ ሕይወታችን ካስገባንባት ቅፅበት አንስቶ፣ ከእግዚአብሔር ጋር አዲስ ግንኙነት ጀምረናል፣ አዲስም ሕይወት አግኝተናል፡፡ አሁን ክርስቶስ በሕይወታችን ያለንን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልጠን እንዲህ ነው፡፡ እኛ፡

  • ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ነን (ሮሜ 5፡1)
  • የእግዚአብሔር ልጅ (ዮሐንስ 1፡12)
  • ሙሉ በሙሉ ይቅር የተባልን (ቆላስይስ 1፡14)
  • ወደ እግዚአብሔር ቀርበናል (ኤፌሶን 2፡13)
  • በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል (ኤፌሶን 1፡13)
  • ከእንግዲህ በጨለማ አንመላለስም (ኤፌሶን 5፡8)
  • የመንግሥቱ አባላት (ቆላስይስ 1፡13-14)
  • በእግዚአብሔር የተወደዱ (1ኛ ዮሐንስ 4፡9-10፤ ዮሐንስ 15፡9)
  • የዘላለም ሕይወት የተሰጠ (ዮሐንስ 3፡16)
  • በእግዚአብሔር ፍቅር የተጠበቅን (ሮሜ 8፡38-39)
  • በእግዚአብሔር ጸጋ የዳንን (ኤፌሶን 2፡8-9)
  • ክርስቶስ በልባችን ይኖራል (ኤፌሶን 3፡17)
  • በእግዚአብሔር የተመረጡ (ኤፌሶን 1፡4፣5)
  • ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርን (ዮሐንስ 5፡24)
  • በክርስቶስ ሕያዋን የሆንን (ኤፌሶን 2፡15)
  • የእግዚአብሔር ጽድቆች (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)
  • በሚንከባከበን እረኛ የምንመራ (ዮሐንስ 10፡27)

ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “… ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም” (ዮሐንስ 6፡37)፡፡ በመቀጠልም “እኔም የዘላለምን ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፣ ለዘላለምም አይጠፉም፣ ከእጄም ማንም አየይነጥቃቸውም፡፡ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፣ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም፡፡ እኔና አብ አንደ ነን” (ዮሐንስ 10፡28-30)፡፡ በማለት እኛን በአስተማማኝ ጥበቃው ስር አድርጎናል፡፡

ከዚህም ባሻገር፣ “በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈፅመው ይህን ተረድቼአለሁና፤” (ፊልጰጵስዩስ 1፡6) እንደተባለለን እንሆናለን፡፡

ኢየሱስ የኃጢአት ዕዳችንን ሁሉ ከፍሏል፣ ስለዚያ ከማሰገንነው፣ ወደ ሕይወታችን ካስገባነውና ሕይወታችን የእርሱ እንዲሆን ከሰጠን፣ እርሱም ልጆቹ ካደረገን፣ ሙሉ ይቅርታን ያደርግልናል በእርሱም ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡

ዝምድናችን የተጠበቀው፣ እኛ በሠራነው ሥራ ሳየይሆን፣ በእግዚአብሔር ባህርይ እና ኢየሱስ በእኛ ምትክ በመሞቱ ምክንያት ነው፡፡ ኢየሱስ ከእኛ ጋር ያለውን ግንኙነት በዋጋ ገዝቶታል፣ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የቆመውንም የኃጢአት ዕዳ አሰወግዶታል፡፡ ኢየሱስ ኃጢአታችንን በመክደኑ ምክንያት እኛ ልጆቹ ሆነናል፣ ይቅር ተብለናል፣ እርሱ በእኛ አድሯል፣ በፊቱም ጻድቃን ተብለን ተቆጥረናል፡፡ የሚያሳዝነው ግን፣ አሁንም ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አሁንም ነገሮችን በእግዚአብሔር መንገድ ከማድረግ ይልቅ በራሳቸን መንገድ ማድረግን እንመርጣለን፡፡ ይህ ግን ከክርስቶስ ጋር ያለንን ዝምድና ዋስትና አያሳጣውም፡፡ በዚህ ዝምድና ያለ ስጋት ተጠብቀን እንኖራለን፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፣ “እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤” (ሮሜ 5፡1)

በኢየሱስ አማካይነት የተገኘው ድነት የእግዚአብሔር ስጦታ ብቻ ነው፣ የምንቀበለውም አንደ ጊዜ በእምነት ነው፡፡ በዚያኑ ቅፅበትም ከእግዚአብሔር ጋር ዘላለማዊ ወደ ሆነ ዝምድና ውስጥ ገብተናል፡፡ ከክርስቶስ ጋር ያለን ዝምድና በግል ቅደስናችን፣ በእምታችን ደረጃ፣ ወይም በመስዋዕቶች ወይም በምናከናውናቸው በጎ ተግባራት አሊያም በሃየይማኖታዊ ምግባር ላይ አይሽከረከርም፡፡ ትኩረታችን በምናከናውነው ተግባር ላይ እንዲሆን እግዚአብሔር አላቀደውም፡፡ ትኩረታችን በኢየሱስ ላይ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ወደዚህ ዝምድና ውስጥ ያመጣን እርሱ ስለሆነ እና እኛንም በዘላለም ሕይወት ሊጠብቀን ታማኝ ስለሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ዝምድና በዓለም ላይ ካሉን ከየትኞቹም ዝምድናዎች የተለየ ነው፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡9 እንዲህ ይላል፣ “ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው፡፡”